ያልተዘመረላቸው ጀግኖች

ዛሬ የአርበኞች ቀን ነውና እኛም ጥያቄ አለን
.

——-የወረ ጃርሶውን ጦረኛ ምን ዋጠው?——-
.
.
ስንቶቻችንስ ይህንን ጉዳይስ አምሰልስለነው ይሆን? ለምንስ የአብቹ ታሪክ በአንድም የኢትዮጵያ ታሪክ ጸሀፊ ቦታ ሳይሰጠው ሰራዊታቸውን አውላላ ሜዳ ላይ በትነውትና ምርጥ አሽከሮቻቸውን አስከትለው ወደ አውሮፓ በባቡር የኮበለለውን ንጉስ ከፈጣሪ እኩል አድርገን መወድሰ ዝማሬን እየተቀኘንለት
ኖርን?
.
“ሐበሽስካ ኦዲየሳ” የተሰኘው የታሪክ መጽሐፍ ወደ አማርኛ እስከ ተመለሰበት 1989 ድረስ አብቹ የሚባል ጀግና ስለመፈጠሩም የሚያውቅ ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ እውነተኛ ጀግኖች በመብራት በሚታሰሱበት በዚያ ዘግናኝ ወቅት ተዓምር የሚመስል ጀብዱ እየፈፀመ ጣሊያንን ሲያርበደብድ የነበረ ጀግና፣ የመከራው ጊዜ ሲያልፍ ስሙ እንኳ ለምን ተረሳ?
የሚገርም ጉዳይ ነው፡፡
.
እኮ አብቹ እንዴት ይረሳል?
በወዶ ዘማችነት ከራስ ካሳ ጦር ጋር ዘምቶ የነበረው ቸኮዝሎባኪያዊው አዶልፍ ፓርለሳክ እንኳ ከዚያ ሁሉ ሠራዊት መሃል እንደ አብቹ በህሊናው ታትሞበት የቀረ ምርጥ ጦረኛ
እንደሌለ የተገለጸለት የወረ ጃርሶው “ልጁ”
በዚያ አስከፊ ሰዓት እንዲህ ዓይነት ተዓምር የሠራ የ16 ዓመት ጉብል መኖሩን የነገረንም ለምን ባእዱ ፓርላክ ብቻ ሆነ፡፡ ብዙ ሰዎች ስለማይጨው ጦርነት ጽፈዋል፡፡ ብዙ የመጻፋቸውን ያህል የንጉሡንና የራሶችን “እንከን አልባ” ታሪክ ለዘመናት ሊነግሩን
ደከሙ እንጂ እንደ አብቹ ያሉ ሳተናዎችን ታሪክ እየመዘዙ ለምን አልነገሩንም ብለን ካልን ምክንያቱ ሌላ ሳይሆን አብቹ ኦሮሞ
በመሆኑ ብቻ ነው።
.
አዎ ስለ አብቹ ማንነት፣ የት ተወልዶ የት እንዳደገ፣ ገና የ16 ዓመት ጉብል ሳለ ስለፈፀመው ተዓምራዊ ጀብዱ፣ በንጉሡና
በራሶች ዘንድ ስጋት ሆኖ ስለመታየቱ፣
የጣሊያኖችንም ሆን የባንዳዎችን ቅስም እየሰበረ ወደፊት ስለመገስገሱ፣ ከማይጨው ሽንፈት በኋላም የሚወደውን አለቃውንና ጓደኛውን ደጃዝማች አበራን እና ሁለት ወዶ ዘማች ፈረንጆችን (አንደኛው የአብቹን
ታሪክ በመጠኑም ቢሆን የጻፈውን አዶልፍ ፓርለሳክ ነው) ተሰናብቶ በጥቁር ፈረሱ ላይ ሆኖ፣ ከሁለት የጦር ሜዳ ጀግኖቹ
(ጀኔራል ወርቁና ጀኔራል ሃብቶም) ጋር ቁልቁል ወደ ዓባይ ሸለቆ ሽምጥ መጋለቡን ፓርላክ ሲያወጋን ቀጣዩን ታሪክ ነጋሪ አልነበረንም
አብቹ ወደ ጃርሶ ወረደ፡፡ከዚያስ? ሃሳቡ ተሳክቶለት በለመደው የጀግንነት ወኔ ጣሊያንን ተፋለመ? ተፋልሞስ ለድል በቃ? ወይስ
በጠላት አረር ሆነ፣ ከማይታወቅ ቦታ ወድቆ የጆቢራ ራት ሆነ? ወይስ መንግስት ቂም ቋጥሮ ቆይቶ እንደ ሌሎች በድብቅ ቀበረው? ለፈፀመው ጀብዱስ ከድል በኋላ መንግሥት ምን ወሮታ ከፈለው? በአብቹና መሰል አርበኞች ለዘውድ የበቁት ንጉሥ እንዴት ረሱት? በአስጨናቂዎቹ የጦርነት ወቅቶች “እሰሩት!
ገንዙት!” ሲሉ የነበሩ ልዑላን ራሶች ከድል በኋላ እንዴት ስሙ እንኳ ትዝ አላለቸውም?
.
ምነው የንጉሱን በቅሎ ራያ ላይ በጥይት መቁሰል የጻፉት ጸሀፍት ነን ባዮች አንባራዶ እና ማይጨው ጠላቱን ያንቀጠቀጠውን ያን የ16 አመት ደቦል እንዴት ዘነጉት?
.
በወቅቱ የጃጀ የመከላከል ሃሳብ ለነበራቸው ለነዚያ ለፈራው ንጉስና አዛውንቶች ባለመታዘዙ ሹመት ሽልማቱ ይቅርበት፤ግዴለም፡፡ ግን እንዴት በስህተት እንኳ ስሙ አይነሳም?
የሃገራችን ታሪክ ጸሐፊዎችስ (በተለይ ስለማይጨው ዘመቻ የጻፉና በግንባሩ የነበሩ) ለምን ንፉግ ሆኑ? አብቹኮ ህይወቱን
አልነፈገንም፡፡
.
ለነገሩ ሰውን ገድሎም ሆነ በቁሙ መቅበር በሀገራችን አዲስ ነገር አይደለም ግን ታሪክን እንዴት መቅበር ይቻላል? አብቹን የመሰለ ብሔራዊ አርበኛ ታሪክስ ከምን ዓይነት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ቢቀበር ነው ፍንጩ እንኳ የታጣው ካልን ታሪክን በመቅበር የዳበረ ልምድ ስላላቸው ነው።
.
እኒያ ትብታብ ከመተብተብ ያላለፉት ጸሀፍት ነን ባይ ደብተራዎች የአብቹን እና መሰሎሉን ታሪክ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የቀበሩት ለኦሮሞ ካላቸው ጥላቻና ፍራቻ በደም ስራቸው ስለሚዘዋወር ነው።

via Gumaa Saqeta

.

Advertisements
Create your website at WordPress.com
Get started